Thursday, July 28, 2016

‘‘ኃያላን እንዴት ወደቁ! የሰልፍም ዕቃ እንዴት ጠፋ!’’ 2ኛ ሳሙ 1፣27፡፡



(ክፍል አንድ)
መጽሐፍ ቅዱስ ከሚነግረን እውነት ውስጥ አንደኛው ኃያላን የነበሩ ሰዎች እንዴት እንደወደቁና በሰልፍ የበረቱትም እንዴት እንደተሸነፉ ነው፡፡ ኃያላን የሚባሉት በሰማያዊው ሀብትና ጸጋ የበረቱትና ብዙ ድንቆችን የፈጸሙት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት ሰዎች ሲሆኑ ሰልፍ ተብሎ የተጠቀሰውም የሚያመለክተው የሰው ልጅ በምድር ላይ ሲኖር የሚያልፍባቸውን የሕይወት ምዕራፎች ነው፡፡ ‘‘በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?’’ እንዲል፡፡ ኢዮ 7፣1፡፡ ክርስቲያኖች ሆነን በዚህች ምድር ላይ ስንኖር በመንፈሳዊውም ሆነ ሥጋዊ ኑሯችን የሚገጥሙን የተለያዩ ተግዳሮቶች ስላሉ እነዚህ ተግዳሮቶች ራሳችንን ለእግዚአብሔር ፈቃድና ሃሳብ የምንለይባቸውና የምንታገልባቸው (የምንዋጋባቸው) ሰልፎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰልፎች በድል የምንወጣባቸውን የሰልፍ ዕቃዎች ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡- ‘‘የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችኹ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ዅሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋራ አይደለምና፥ ከአለቃዎችና ከሥልጣናት ጋራ ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዢዎች ጋራ፥ በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሰራዊት ጋራ ነው እንጂ። ስለዚህ፥ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ዅሉንም ፈጽማችኹ ለመቆም እንድትችሉ፥ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ዅሉ አንሡ። እንግዲህ ወገባችኹን በእውነት ታጥቃችኹ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችኹ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችኹ ተጫምተው ቁሙ፤ በዅሉም ላይ ጨምራችኹ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ዅሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቍር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።’’ ኤፌ 6፣11-17፡፡ በሰልፍ ውስጥ መውደቅና መሸነፍ የምንለው ከእግዚአብሔር ምክርና ፈቃድ ውጪ መጓዝና ፈቃዱን መፈጸም አለመቻል፣ እንደቃሉ አለመኖር፣ በምድራዊ ሐሳብና በስጋዊ ምኞት መሸነፍ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራስን ደስ ማሰኘት . . .    እንደሆነ ታሪካቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ከተመዘገበ የተለያዩ ሰዎች ሕይወት እንማራለን፡፡ ቅዱሳን የምንላቸው በኑሯቸው ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙና ፈቃዱን ያገለገሉ ሰዎች እንደሁኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ‘‘ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም፡፡ ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና’’ ዕብ 11፣5፡፡ ሄኖክ ሞትን እንዳያይ የተወሰደው በኑሮው ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘቱ ስለተመሰከረለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን በኑሯችን ሁሉ ደስ ማሰኘት ካልቻልን በሰልፉ ውስጥ ተሸናፊዎች እንሆናለን፡፡
በእርግጥ ብዙ ኃያላንና ብርቱዎችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እናገኛለን፡፡ ብዙ ብርቱዎችና ኃያላን እግዚአብሔር ስላገዛቸውና ስለረዳቸው ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን በእግዚአብሔር ስም እንዳደረጉም እናነባለን፡፡ ታናሹ ብላቴና ዳዊት የጦሩን ሰው ጎልያድን በወንጭፍ እንዳሸነፈው (1ኛ ሳሙ 17)፣ ጌድዮን ሦስት መቶ ሰዎችን ብቻ ይዞ ብዛታቸው እንደ አንበጣ የኾነ ምድያማውያንና ዐማሌቃውያንን፣ የምሥራቅንም ሰዎች እንዳሸነፈ (መሳ 7)፣ ቅዱስ ጴጥሮስ በአንዲት ቀን ስብከት ሦስት ሺህ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ መንግስት እንዳፈለሰ ( ሐዋ 2)፣ ቅዱስ ጳውሎስ በልብሱ ጨርቅ እንኳን ሳይቀር ብዙ ድንቆችንና ተአምራትን ያደርግ እንደነበር (ሐዋ 19) . . . ይነግረናል፡፡ እንደኛ ሰዎች ቢሆኑም ነገር ግን አካሄዳቸው እግዚአብሔርን ደስ ስላሰኘው በእጃቸው ብዙ ድንቅና ተአምራት ሊደረግ እንደቻለ እናነባለን፡፡ ከሐዋርያትም በኋላ የተነሱ የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ሊቃውንት ሕይወታቸውንና ፈቃዳቸውን ሁሉ ለእግዚአብሔር መስጠት ስለቻሉ እግዚአብሔር አምላካችን ብዙ ተአምራትንና ድንቆችን በእነርሱም ላይ አድሮ ፈጽሟል፡፡ በቅርቡ ዘመን ታሪክም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የለዩና ፈቃዳቸውን ለፈቃዱ መተው የቻሉት ቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችንም ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገው ብዙ ተአምራትን እንደፈጸሙ እናነባለን፡፡ በእኛው ማህበረሰብ ውስጥ የተፈጠሩ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን ከእግዚአብሔርና ከተቀደሰ ሕይወታቸው የተነሳ ብዙ ድንቆችን እንዳደረጉ ታሪክ እንኳን ሳይቀር ይመሰክርልናል፡፡
ተአምራትና ድንቅ ለእግዚአብሔር የባህርይ ገንዘቦቹ ናቸው፡፡ እርሱ ሁሉን ይችላልና፣ የሚሳነውም ነገር የለምና በቅዱሳኑ እያደረ ኃይሉንና ተአምራቱን ይገልጣል፡፡ ቅዱሳኑ በሕይወታቸው ደስ አሰኝተውታልና፤ በኑሯቸውም ሁሉ ፈቃዱንና ሐሳቡን ተከትለው የራሳቸውን ፈቃድና ሐሳብ መተው ችለዋልና እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ በእነርሱ ሊጠራ አያፍርባቸውም፡፡ ዕብ 11፣16፡፡ በዚህም የተነሳ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደምናነበው፣ ከቤተ ክርስቲያን ታሪክም አንደምንረዳው ብዙ ቅዱሳን ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብር መግለጥ ችለዋል፣ ብዙዎችን ወደ መዳን መንገድ መርተዋል፣ በተአምራትና በድንቅ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰብከውታል፡፡ በዚህ ሁሉ ወስጥ ግን ‘‘የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን’’ እያሉ ክብሩን ሁሉ ለአምላካቸው ስለተዉ ከጅማሬያቸው የሚልቅን ፍጻሜ ሊቀበሉ ችለዋል፡፡ 2ኛ ቆሮ 2፣7፡፡ ‘‘ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው’’ እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በእጃቸው የተደረገው ድንቅና ተአምር ሁሉ ከእግዚአብሔር መሆኑን ተረድተው እግዚአብሔርን ብቻ እንጂ ራሳቸውን ስላላከበሩ ቢወድቁ እንኳን እየተነሱ በኋላ ዘመን ለምንነሳ ክርስቲያኖች ሁሉ ሳይቀር አርአያና ምሳሌ ሆኑልን፡፡ 2ኛ ቆሮ 12፣7፡፡
እውነተኛው የክርስትና ትምህርት እንዲህ ያለ ነው፡፡ በነገር ሁሉ እስከ ሞት የወደደንን መድኃኒታችንን ደስ ማሰኘት፤ የእርሱንም ፈቃድ ብቻ መፈጸምና ማገልገል፡፡ ክርስትና የሚፈልገው ራስን ማክበር ሳይሆን ‘‘እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል’’ ማለትን ነው፡፡ ዮሐ 3፣30፡፡ እስኪ በዘመናችን ካሉ ክርስቲያኖችና አገልጋዮች መካከል ‘‘እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል’’ የሚል ማን ነው? በአገልግሎትና በወንጌል ሽፋን የራሱን ፈቃድ ለማቆም የማይሞክር ማን ነው? በዚህ ዘመን እየሆነና እኛም እያየነው ያለነው ስለክርስቶስና ስለወንጌል ሲሉ ለመተውና ለመሸነፍ የተዘጋጁ አገልጋዮችንና ክርስቲያኖችን ሳይሆን ማሸነፋቸውን በክርስቶስ ስምና በመንፈሳዊነት ሽፋን ለማጽደቅ የሚሞክሩትን ነው፡፡ ከክርስቶስ ግን እንዲህ አልተማርንም ክብር የሚገባው እርሱ፤ ክብርም ደግሞ የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከልዑል ቦታው ወርዶ በበረት ሲያድር፣ በግርግም ሲተኛ፣ አምላከ ሆኖ ሳለ ሰው ሲሆንና በምድር ላይ በደካማ ማንነት ሲገለጥ መዳናችንን በዝምታ ነው የሰራልን፡፡ መጽሐፍ ‘‘አፉን አልከፈተም’’ እንዲል በጎውን ከማድረግ ባለፈ በአንደበቱ ሀሰት አልተገኘበትም፣ በከሳሾቹም ፊት አንዳች አልተናገረም፡፡ እርሱ ዝም ብሎ ነበር ሥራውን ይሰራ የነበረው፡፡ ኢሳ 53፣7፤ ሐዋ 8፣32፡፡ እኛ ግን ስለራሳችንና ስለታላቅነታችን አውርተን አንጠግብም፣ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ ስለሰራው ሥራ እርሱን ሳይሆን ራሳችንን ልናከብር እንወዳለን፡፡ እርሱ ግን እጅግ ታላቅ ሲሆን ራሱን አላከበረም፡፡ ‘‘እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ከንቱ ነው፤ የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው’’ እንዳለ ክብርን ከላይ ከአባቱ ዘንድ እንጂ ከምድር አልፈለገም ነበር፡፡ ዮሐ 8፣54፡፡ ከክርስቶስ የተማርነው ይህንን ነው፤ ዝም ብሎ የሰማዩን አባታችንን ፈቃድ መፈጸም፣ የእርሱን ሃሳብ ማገልገል፡፡ እኛ እንደምንፈልገው ሳይሆን እርሱ እንደሚፈልገው ማድረግ፤ እኛ እንዳሰብንና እንደፈቀድን ሳይሆን እርሱ እንዳሰበና እንደፈቀደ መፈጸም፤ በእሺታ መንፈስ መታዘዝ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጸብና ክርክር፣ ቁጣና አድመኝነት፣ ጥልና መለያየት፣ ራስን ማክበርና ደስ ማሰኘትስ ከወዴት ይመጣሉ?
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ‘‘ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ፡፡’’ ማለት ካልቻልን እውነተኞች የእግዚአብሔር መንግስት ሰራተኞች ልንሆን አይቻለንም፡፡ ሐዋ 20፣24፡፡ መንፈሳዊነት ለእግዚአብሔር ሐሳብ መሸነፍ ነው፣ የእግዚአብሔርንም ሥራ በመንፈስና በትህትና መሥራት ነው፡፡ በስጋዊነት፣ በስሜትና በስጋዊ ጥበብ መድከም፤ በዚህም ለማሸነፍ መጣር አይደለም፡፡ ‘‘አዎን፥ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ተጐዳሁ፥ ክርስቶስንም አገኝ ዘንድ፥ በክርስቶስም በማመን ያለው ጽድቅ ማለት በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለው ጽድቅ እንጂ ከሕግ ለእኔ ያለው ጽድቅ ሳይሆንልኝ፥ በእርሱ እገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቆጥራለሁ፡፡’’ ይህ ነው እንግዲህ ክርስትና፡- ከእኛና ከዚህች ምድር የሆነውን ሁሉ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታችን እውቀት ብለን ጉዳት እንደሆነ መቁጠር፣ በእምነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለውን፤ በመንፈስ ከምናመልከው አምላካችን የሚደረግልንን ጽድቅ መጠበቅ፣ በእርሱ እንገኝ ዘንድ ሁሉን እንደጉድፍ መቁጠር፡፡ ፊል 3፣8-9፡፡ እንዲህ የሚያደርጉ መንፈሳውያን ባሉበት ጸብና ክርክር፣ ጥልና መለያየት፣ ነቀፌታና ፈራጅነት፣ ወንድምን መርታትና ማሸነፍ ከወዴት ይመጣሉ? በእርግጥም ላይኛይቱ ጥበብ መንፈሳዊትና ፍጽምትም ናት፣ ከስጋዊ ሐሳብና ምክርም በእጅጉ የራቀች ናት፣ ወንድምን የምትወድና ደስ የምታሰኝም ናት፡፡ ‘‘ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት፡፡’’ ያዕ 3፣17፡፡
አሁን ባለንበት በዚህ ዘመን የእግዚአብሔር አገልጋዮችና የወንጌል ሰባኪዎች ነን ብለን ራሳችንን የገለጥን አንዳንድ ሰዎች አለን፡- ቃሉን ስናስተምር ደስ እናሰኝ የነበርን፣ ብዙዎችን ወደ መንጋው የቀላቀልን፣ ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የደከምን፣ ስለ ፍቅር ያስተማርን፣ ስለ ይቅርታ የሰበክን፣ ስለ አንድነት የመከርን፣ በእምነት ስለመጽናት የተናገርን፣ እንደዋኖች ሆነን ራሳችንን የገለጥን . . . ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ለሌሎች ባስተማርነው ቃል መጽናት ተስኖን የወደቅን፣ ፍቅርን እንዳላስተማርን በጥላቻ ውስጥ ሆነን የተገኘን፣ ስለ ይቅርታ እንዳልሰበክን ይቅርታ ለማድረግ የሰነፍን፣ ስለ አንድነት እንዳልመከርን መለያየትን ስንዘራ የተደረሰብን፣ በእምነት ስለመጽናት እንዳልተናገርን ከእምነት መንገድ ወጥተን የሚያስነቅፍ ነገር የተገኘብን . . . ብዙ ታላላቆችና ኃያላን ዛሬ ላይ እንደትናንቱ ሆነን አልተገኘንም፡፡ ትናንት የነበረን በጎነት፣ ቅንነት፣ መንፈሳዊ ቅድስና፣ ትህትና፣ እግዚአብሔርን መፍራት . . . ዛሬ ላይ አልተገኘብንም፡፡ ስለ ሃይማኖት ሰውነታችን ብዙዎች እንዳልተከራከሩልን ዛሬ ላይ ለብዙዎች የመሰናክል ደንጊያ ሆነን የሃማኖታችንን ፍሬ ለሌሎች ማሳየት ያቃተን፤ ግን ደግሞ አሁንም ራሳችንን የሃይማኖት አገልጋዮች አድረገን የምንቆጥር አለን፡፡ በእርግጥ ግን ከትናንት ኃያልነታችን ዛሬ እንዴት ልንወድቅ ቻልን? መንፈሳዊነታችንስ እንዴት ሊጠፋ ቻለ?
ይቀጥላል . . .

የኤጲፋንዮስ ቅዳሴ



(ክፍል አንድ)      
  • እግዚአብሔር በገናንነቱ ገናና ነው፤ በቅድስናው የተቀደሰ ነው፤ በምስጋናው የተመሰገነ ነው፤ በክብሩም የከበረ ነው፡፡
  •  ከመቼ ወዲህ የማይሉት ቀዳማዊ ነው፤ እስከዛሬ የማይሉት ማእከላዊ ነው፣ እስከዚህ የማይሉትም ደኃራዊ ነው፡፡
  • ለአነዋወሩ ጥንት የለውም፤ ለአኳኋኑም ፍጻሜ የለውም፤ ለዘመኑ ቁጥር የለውም፤ ለውርዝውናውም ማርጀት የለበትም፤ ለኃይሉም ጽናት ድካም የለበትም፤ ለመልኩ ጥፋት የለበትም፡፡ ለፊቱ ብርሃንም ጨለማ የለበትም፡፡
  • ለጥበቡ ባሕር ድንበር የለውም፤ ለትእዛዙም ይቅርታ መስፈርት የለውም ለመንግሥቱ ስፋት ዐቅም ልክ የለውም፣ ለአገዛዙም ስፋት ወሰን የለውም፡፡
  • በኅሊና የማያገኙት ሥውር ነው፤ በልቡናም የማይረዱት ምጡቅ ነው፤ አንሥርት የማይደርሱበት ረጅም ነው፤ ዓሣዎች የማይዋኙበት ጥልቅ ነው፡፡
  • ከተራሮች ራስ ይልቅ ከፍ ያለ ነው፤ ከባሕር ጥልቅነት ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ነገሥታት የማይነሳሱበት ጽኑ ነው፤ መኳንንት የማይቃወ አሸናፊ ነው፡፡
  • የጥበበኞችን ምክር የሚያጠፋ ጥበበበኛ ነው፤ የሚመክሩትን ሰዎች አሳባቸውን የሚያስረሳ ዐዋቂ ነው፤ የጸኑ ልጓሞችን የሚፈታ ኃያል ነው፤ የኃጥአንን ጥርሶች የሚያደቅ፣ የትእቢተኞችንም ክንድ የሚቀጠቅጥ ብርቱ ነው፡፡
  • የግብዞችን ፊት የሚያዋርድ ክቡር ነው፤ የዝንጉዎችን ብርሃን የሚያርቅ ከሃሊ ነው፡፡
  • ባልንጀራ የሌለው አንድ ነው፤ ዘመድ የሌለው ሥሉጥ ነው፤ ሰማ ይጠፋሉ፤ የብስም ትጠፋለች፤ ሁሉም  እንደ  ልብስ ያረጃል፡፡ እርሱ ግን እስከ ዘለዓለሙ  እርሱ ነው፡፡
  • የባሕር መመላለሷ ድንቅ ነው ድንቅስ በልዕልናው እግዚአብሔር ነው የሚመስለው የለምከፍጥረትም ሁሉ ከአማልክትም ልጆች ሁሉ የሚተካከለው የለም፡፡ እርሱ ብቻ አምላክ ነው እርሱም ብቻ ጌታ ነውፈጣሪም እርሱ ብቻ ነውሪም  እርሱ ብቻ ነው፡፡
  •  ስላሰበው ጥበብ እረዳት አይሻም ስለ ወደደውም ሥራ መካር አይሻም፡፡ ሳይሆን ቀድሞ እንደ ሆነ አድርጎያልተደረገውንም  እንደ ተደረገ አድርጎ ሁሉን ያውቃል፡፡
  • ሳይጠይቅ ሊናን ይመረምራልሳይመረምር ልቡናን ይፈትናልያለመብራት በጨለማ ያለውን ያያል፡፡
  • ጻድቁን ጽድቅን ሳይ ያውቀዋል ኃጥኡንም ኃጢ ሳይ ያውቀዋልልበኞችን ከአባታቸው ወገ(አብራክ) ሳይወጡ  ያውቃቸዋልኃጥአንንም  ከእናታቸው ጸን ያውቃቸዋል፡፡
  • የሚሸሸገው የለም የሚሰወረውም የለምርሱም  የሚሰወር የለምሁሉ ርሱ ዘንድ የተገለጸ ነውበዓይኖቹም ፊት ሁሉ የተዘረጋ ነው፡፡ ሁሉ በመጽሐፉ  የተጻፈ ነውሊናውም ሁሉ የተጠራ ነው፡፡
  • ቁጥር የሌላቸው ታላላቆችን መመርመር የሌለባቸውን የተደነቁ የከበሩ ራዎችን ራል:: ራው ካየነው  ይልቅ እጹብ ነውኃይሉም  ከሰማነው  ይልቅ ድንቅ ነው  ጌትነቱም  ከነገሩን ይልቅ ድንቅ ነው፡፡
  • ከጨለማ ለይቶ ብርሃንን ፈጠረ ደመናውን መለየት ያውቃል፡፡ ውን እንደወደደ ይከፍለዋልየተመረጡትን በደመና ውራል፡፡
  • ምድርን ፈጠራት መጠኗንም  አዘጋጀፍጻሜዋንም  እንደምንም  ተከለ ማዕዘኗንም አጸና፡፡
  • ባሕርን ከእናቷ ሆድ በወጣች ጊዜ በበሮች አጠራት፡፡ ልብሷንም ደመና አደረገላትበጉም ጠቀለላት ወሰን አደረገላትስጧም መዝጊያዎችንና ቁልፎችን አደረገላት፡፡ ‘‘እስከዚህ ድረሺከወሰንሽም  አትተላለፊ ማዕበልሽ በውስጥሽ ይመላለስ (ይነቃነቅ) እንጂ’’ አላት፡፡
  • በበላይዋ ላይ የንጋት ብርሃን ተዘጋጀየአጥቢያ ኮከብም ትእዛዙን ዐወቀ፡፡ እርሱ ከምድር ጭቃን ሕያው የሆነውን ፈጠረ፡፡ በምድርም ላይ እንዲነጋገር አደረገው፡፡
  • እርሱ እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ፡፡ በጥልቅ ፍለጋም  ተመላለሰ፡፡
  • ከግርማው  የተነሳ የሞት ደጆች ይከፈታሉየሲኦል በሮችም ባዩት ጊዜ ይደነግጣሉ፡፡ ከሰማይ በታች ያለውን ስፋቱን ከሰማይ በላይ የሚሆነውንም  እርሱ ያውቀዋል፡፡
  • ርሱ ትእዛዝ ዋግ ከመዝገቡ ይወጣል፡፡ ከሰማይ በታች ያለ አዜብ (ነፋስ ) ይመላለሳል፡፡ ዝናምን በምድረበዳ ያጸናዋል ሰው በሌለበትና የሰው ልጅ በማይኖርበት ይዘንም ዘንድ፡፡
  • እርሱ የውውን መፍሰሻ ወሰነ ክረምትንም በያመቱ ይከፍታል በጋውንም በጊዜው ጊዜ ያመጣዋል፡፡ደመናውንም በቃሉ ይጠራዋል ውኃ  እየተንቀጠቀጠ  ይመልስለታል፡፡
  • ብልጭልጭታውንም እርሱ ይልከዋል እርሱም ይሄዳል ‘‘ምንድር ነው?’’ እያለ ይመልስለታል፡፡ እርሱ ደመናን በጥበቡ ይቆጥረዋል፡፡ ሰማይን (ጠፈርን ) ወደ ምድር ያዘነብለዋል፡፡
  • እርሱ ብቻ የአርያምን ኃይል ለበሰ በምስጋናና በክብር ተጌጠ፡፡
  • እሳታውያን ኪሩቤል ብርሃን የለበሱ ሱራፌልም እርሱን ያመሰግናሉ፡፡ በማያርፍ ቃል ዝም በማይል በማይደክምም አንደበት ሁሉም ተባብረው ተሰጥዎ ባለበት ባንድ ቃል ‘‘የጌትነትህ ምስጋና በሰማይ በምድር የመላ ፍጹም  አሸናፊ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር’’ ይላሉ፡፡
  • ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የጌትነትህ ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው፡፡
  • ሁሉ ርሱ ነውሁሉም  ስለርሱ ነውሁሉም  ርሱ ነውሰማይ ርሱ ነውከሰማያት በላይ ያለ ሰማይም  ርሱ ነውየአርያም ስፋት የክብሩ ዙፋን ነውየምድርም ስፋት የእግሩ መመላለሻ ናት፡፡
  • ፀሐይ ርሱ ነውጨረቃም ርሱ ነውከዋክብትም የእጁ ሥራ ናቸው ደመናት መልክተኞቹ ነፋሳትም  ረገላዎቹ ናቸውእሳትም  የቤቱ ግርግዳ ነው፡፡
  • የቤቱ ጠፈር ውኃ ነውየዙርያውም ጸፍጸፍ የበረድ ሰሌዳ ነውድንኳኖ ብርሃናት ናቸው፡፡ የመሰወሪያ መጋረጃውም  የብርሃን መብረቅ ነውመመላለሻውም በአየር ነው ::
  • የመናገሩ ድምፅ በብልጭልጭታ ያለ ነው፡፡ የነጎድጓዱ ቃል ረገላዎች አለ፡፡ ባሕር ባሪያው ናት የወንዝ ፈሳሾች ተገዥዎቹ ናቸው፡፡ ቁር አስሐትያም  ፈቃዱን የሚ ናቸው፡፡
  • ከምድር ዳርቻ ደመናውን ያወጣልመብረቅንም  በዝናም ጊዜ አደረገ ዝናምንም  እንደ መሽረብ ነጠብጣብ ያፈሳል ጉምን እንደ አመድ ይበትነዋል በረድንም  እያጠቃቀነ ያወርዳልለእንስሳም ሣሩን ያለመልማል፡፡
  • እንዳሰበ ያደርጋልእንደ ጀመረም  የጀመረውን ይፈጽማል እንደወደደም ያከናውናል፡፡ ያሳዝናል ደስ ያሰኛል ያደያል ባለጸጋም ያደርጋል፡፡ ያዋርዳል ያከብራል ይገድላል ያድናልም ድውይ ያደርጋል ይፈውሳልም  ይኮንናል ያጸድቃልም፡፡
  • የወደደውን ይምራልሊያስጨንቀው  የወደደውን ያስጨንቃልየሚምረውን  ይምረዋል፡፡ ይቅር የሚለውን ይቅር ይለዋል፡፡