·
እግዚአብሔር
አብ አንድ ልጁን የሰደደው ባል በማታውቅ በወለት ሥጋ ያድር ዘንድ ነው፡፡ ሕፃናትን የሚፈጥር
እርሱ ሳይወሰን በማኅፀን ተወሰነ፡፡ አምላክ ሲሆን
ሰው ሆነ፤ እሳተ መለኮትም ሲሆን ተወለደ፣ አደገ፤ በጌጥና በክብር
አይደለም፡፡ እንደ ድሆች ልጆች ለዘመዶቹ እየታዘዘ በብዙ ተግሣጽ አደገ
እንጂ፡፡
·
ከኀጢአት ንጹሕ ሲሆን
ባሪያ ያጠምቀው ዘንድ ራሱን አዘነበለ፡፡ ውኃን ጠጅ እስከማድረግ ድረስ ተአምራትን
አደረገ፤ በምድረ
በዳም ለብዙ ሰዎች እስኪያጠግብ ድረስ፡፡
·
ወዮ በዚያ
ጊዜ የነበሩ ትውልድ እንዳያዩት አይናቸው ታወረ፤ እንዳይሰሙት ጆሯቸው ደነቆረ፤ እንዳያውቁትም ልቡናቸው ተሸፈነ፡፡ ኀጢአትን ይቅር የሚለውን እርሱን ዕሩቅ
ብእሲን አስመሰሉት፡፡ በመኳንንት ላይ የሚፈርደውን ፈረዱበት፡፡
·
ከእነርሱም ወገን አስራ ሁለት ሐዋርያትን
መረጠ፤ ከእነርሱም ጋራ ተመላለሰ፡፡ የቁርባን ምሥጢረ ሥርዐትንም አሳያቸው፡፡
·
በዚያች ሌሊት
ያዙት በነጋም ጊዜ የአይሁድ መምህሮችና የካህናት አለቆች ከገዥ ከጲላጦስ ጋራ ሊፈርዱበት በአደባባይ ተቀመጡ፡፡
·
እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት፤ እንደ
የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፡፡ ሊፈርዱበት በአደባባይ ተቀመጡ፡፡ የመላእክት ሰራዊት በመፍራት በመንቀጥቀጥ የሚቆሙለትን በፊታቸው አቆሙት፡፡
·
ክፉ ባርያ
እርሱን ያልበደለውን ይጸፋው ዘንድ እጁን አጸና፡፡ የመላእክት አለቆች በፍጹም ድንጋፄ
ለሚሰግዱለት ለእርሱ በትዕቢት ይሰግዱ ዘንድ አጎነበሱለት፡፡
·
የሕይወትን ራስ የሾህ ዘውድ ደፉበት፡፡ ብርሃንን
እንደ ልብስ የሚጎናጸፈውን ልብሱን ገፍፈው ቀይ ግምጃ አለበሱት፡፡
·
ወደሚሰቅሉበት
ስሙ ቀራንዮ ወደሚባል አገር ወሰዱት፡፡ መስቀሉን አሸከሙት፤ ኢየሱስም መስቀሉን በመሸከም ደከመ፣ ወዛ ከባድ ነውና፡፡ ከወንበዴዎች
ጋራ ቆጠሩት፡፡ ወደ እንጨትም አውጥተው ምህረት የሌለው ስቅለትን እንደ
ሕጋቸው ሰቀሉት፡፡
·
አዳምን የፈጠሩ እጆች ወዮ በመስቀል
ቀኖት ተቸነከሩ፡፡ በገነት የተመላለሱ እግሮች ወዮ በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡፡
·
በአዳም ፊት
የሕይወትን መንፈስ እፍ ያለ አፍ ወዮ ከሐሞት ጋራ መጣጣንና ከርቤን ጠጣ፡፡
·
ኢየሱስ በሕማሙ (በመከራው ) አሰምቶ ጮኸ፤ ወደ አባቱ
ጮኸ፡፡ ራሱን ዘለስ አደረገ፤ ያን ጊዜ ነፍሱ ወጣች (ተለየች ) ፡፡
·
ለእርሱ ብለው
ባሰሩት በጥቁር ጦር ጎኑን ወጉት፡፡ ከእንጨት አውርደው በመቃብር አኖሩት፡፡ በእነርሱ መቃብር
ያኖሩት አይደለም፡፡ ከከተማ ውጭ ሶስት
ክንድ በሚሆን በስደተኛ መቃብር ነው እንጂ፤ በደንጊያም ገጠሙት፡፡
·
በዚያም ሳለ ወደ ባሪያው ወደ አዳም፤ ወደ ልጆቹም
ሁሉ ጮኸ፡፡
·
ዳግመኛም
የትንሣኤውን ክብር ይገልጽ ዘንድ ጥቂት ብርሃኑን አወጣ፤ መቃብሩን የሚጠብቁትንም ጣላቸው፡፡
·
በሦስተኛይቱ ቀን ተነሳ፡፡ በተረጋገጠች
ቀን ደቀመዛሙርቱ ወዳሉበት ገብቶ የጎኑን መወጋት፣ የእጆቹን መቸንከር አሳያቸው፡፡ የመንግሥተ
ሰማያትን ነገር እያስተማራቸው ከእነርሱ ጋር ኖረ፡፡
·
በዐርባኛውም
ቀን ወደ ላከው አብ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ዳግመኛም ይመጣል፤ በትህትና የሚመጣ አይደለም በወለደው በአብ ጌትነት፤ በሚያስፈራ ስልጣን ከቅዱሳን መላእክቶቹ
ጋራ በሰማይ ደመና ነው እንጂ፡፡
·
አቤቱ ሞትህን ቅድስት ትንሣኤህንም
እንናገራለን፡፡ እርገትህን ዳመኛም መምጣትህን እናምናለን፤ እናመሰግንሃለን እናምንሃለን፡፡ ጌታችንና አምላካችን ሆይ እንለምንሃለን፤ እንማልድሃለንም፡፡
·
አቤቱ ይቅርታህ
ለእኛ ትደረግልን፡፡ በአንተ እንዳመንን መጠን፡፡
·
መሰብሰቢያችንም እንደ ደቀ መዛሙርትህ መሰብሰብ
ይሁን፡፡ የእነርሱ ፈጣሪ አንተ ነህ፡፡ የእኛም አንተ ነህ፡፡ያንጊዜ የነበርህ አንተ ነህ፤ ዛሬም ያለህ አንተ ነህ፡፡
·
ሰማያት ያንተ
ናቸው፤ ምድርም ያንተ ናት፡፡ ጻድቃን ያንተ
ናቸው፤ ኃጥአንም ያንተ ናቸው፡፡ ብዙውን ኀጢአት ይቅር
ትላለህና፡፡ ጥቂቱን ስለ ጽድቅ ታቆማለህ፡፡ ለመዳንም ምክንያት ትሻለህ፡፡
·
ከርሱ ለሚቀበሉ ሁሉ አንድ አድርገህ
ስጣቸው፡፡ ለሚቀበሉት ንጽሕን ይሆናቸው ዘንድ፡፡ ለሚቀበሉትም መመረጫ ይሆናቸው ዘንድ፡፡ እርሱን በማየት የኀጢአት እሾህነት ይቃጠል ዘንድ፤ አበሳ ትነቀል በደልም ትጠፋ ዘንድ፤ ነፍስም ከበደልዋ ፈጽማ ታርፍ ዘንድ፡፡
·
የብርሃን
ደጅ ይገለጥ፡፡ የብርሃን በርም ይከፈት፡፡ ቅዱስና ሕያው
የሚሆን መንፈስም ይላክ፡፡ አኗኗሩ ከተሰወረ ቦታ ይውረድ ይምጣም፡፡
·
ከሁሉ በላይ የምትሆን የአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን የማህበሯን
ፍጻሜ ማራቸው፡፡ ይቅርም በላቸው፡፡ይልቁንም ይህንን ምስጢር ለማገልገል የእኔን ንዴት የመረጡትን ማራቸው፡፡ ይቅርም በላቸው፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
·
የአንተ በሚሆን
በመንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ መሆንን ስጠን፡፡ በዚህም ጵርስፎራ (በስጋው
በደሙ) አድነን፡፡ ለዓለሙ ሁሉ በምትሆን በአንተ ለዘለዓለሙ ሕያዋን
እንሆን ዘንድ፡፡
·
የእግዚአብሔር ስም ምስጉን ነው፤ በእግዚአብሔር
ስም የሚመጣውም ምስጉን ነው፡፡ የጌትነቱም ስም ይመስገን ይሁን ይሁን የተመሰገነ ይሁን፡፡
·
ዳግመኛም
ዓለምን የያዘውን ከኀጢአታቸውም ቤዛ የሆናቸውን
እርሱን እንማልደዋለን፡፡ ከቅድስት ድንግል የነሳኸው ሥጋ የእኛ ሥጋ እንደሆነ፤ ከሰማይ ያወረድከው እንዳይደለ አስብ፡፡
·
ከቅድስት ድንግል የነሳኸው ሥጋ የማሠሪያ መዘጋትን የተሸከመ ሥጋ እንደሆነ አስብ፡፡
·
ከቅድስት
ድንግል የነሳኸው ሥጋ የታመመው፤ የሞተውም እንደሆነ አስብ፡፡
·
ከቅድስት ድንግል የነሳኸው ሥጋ በሶስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ
የተነሳው ሥጋ እንደሆነ አስብ፡፡
·
ከቅድስት
ድንግል የነሳኸው ሥጋ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ያረገ በአባቱም ቀኝ የተቀመጠው
እንደሆነ አስብ፡፡ዳግመኛም አምላካችን እግዚአብሔር በዚህ ሥጋ ከመለኮቱ
ኃይል ጋራ
ይመጣል፡፡
·
ነፍሳችሁን መርምሩ ሰውነታችሁንም
አንጹ፡፡ የእኛ ወገን ማንም በበደልና በኀጢአት ብዛት አይታመም፡፡
·
የእግዚአብሔር
በግ አማኑኤል እነሆ ዛሬ ከእኛ ጋራ በዚህ ማዕድ ላይ
አለ፡፡ እነሆ ብርሃን አብ ከልጁ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ አለ፡፡
·
ቤተክርስቲያንን የሚጎበኙ የብርሃን
መላእክት እነሆ አሉ፡፡ ነፍሳችሁን መርምሩ ሰውነታችሁንም አንጹ፡፡ ከእኛ ወገን ማንም ማን አይታመም፡፡ የበደል አለ፤ የኀጢአትም አለ፤ ይህንንም ምስጢር ለመቀበል የተገባን
እንሆን ዘንድ ኅሊናችንን ንቁሕ እናድርግ ለዘለዓለሙ፡፡
·
በልጅህ በወዳጅህ
በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ጌትነትህ ገናንነት ፊት ያቀረብከን አቤቱ እናመሰግንሃለን፤ ለአንተ ጌትነትና
ክብር ምስጋናም ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
·
ያ ቃል ቀድሞ የነበረ ነው፡፡ ያ ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ያ ቃል ሥጋ ሆነ በእኛም አደረ፡፡ ለአባቱ እንደ አንድ ልጅ ክብር የሚሆን ክብሩን
አየን፡፡ ያ ቃል ወደ ወገኖቹ መጣ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፡፡
·
የተቀበልነው
እኛ ሶስት መቶ አስራ ስምንቱ ነን፡፡ ሃይማኖትን ያቀናን ሙሽራዋ አምላካችን እግዚአብሔር የሆነ
የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሕግ የሰራን፡፡
·
አይኖቻቸው ብዙዎች የሚሆኑ ኪሩቤል፣ ክንፎቻቸው ስድስት የሚሆኑ ሱራፌል
የሚከቡህ አንተ ነህ፡፡
·
አዳምን በአንተ
አርአያና አምሳል የፈጠርከው ሆይ እሳትን በውኃ ላይ ያሰፈርከው ሆይ ጨለማ የማይጨልምበት
ሌሊትም የማይሰወረው ሆይ ወደዚህ ምስጢር ፊት ያቀረብከን አንተ ነህ፡፡ ለአንተ ጌትነት
ክብር ምስጋናም ይገባል ለዘለዓለሙ፡፡
·
አቤቱ አምላካችንና መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ባርከን ቀድሰን፡፡ ያለ ኀጢአት ያለ ርኩሰት በፍጹም ደስታ ወደ
ቤታችን ለመሄድ የበቃን እንድንሆን አድርገን፡፡
·
ከክብርት
ማዕድ የተቀበልነው ሥጋህና ደምህ የሚያድነን ይሁንልን፡፡
·
አቤቱ ቅዱስ መንፈስህንም ላክልን ወደ ጽድቅና ወደ ሕይወት
ጎዳና ይመራን ዘንድ፡፡
·
የሕያው እግዚአብሔር
ልጅ ሥጋውንና ደሙን በዚህ ዓለም ሰራ፡፡ ከእርሱ በልተን ከእርሱ ጋር
እንኖር ዘንድ፡፡
·
ሕያውና ቅዱስ በሚሆን መሰዊያህ
ዘንድ በምሕረትህ ወደ አንተ አቅርበን፤ የእግዚአብሔር ባሮች የልዑልም ማረፊያ (ማደሪያ )እንባል ዘንድ፡፡ ሁላችንም ወደርሱ እንቅረብ፤ በልመናና
በስግደት፤ በጸሎትና በንጽህና፤ በማመን ከፊቱ እንደርስ ዘንድ፡፡
·
በየጊዜው
ሁሉ፣ በየሰዓቱም ሁሉ ጸሎትንና ልመናን በሚያሳርጉ በካህናት እጅ የተቀበልነው
ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ለሕይወት፣ ለተስፋ፣ ለመድኃኒትና ለኀጢአት ማስተስረያ፣ ከሙታንም ተለይቶ ለመነሳት ይሁነን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
No comments:
Post a Comment